Tender Detail

Tender Details

  • Company በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ባሌ ዞን : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 13 34 16 20
  • Website
  • Deadline29 Aug 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 (አምስት መቶ) የማይመለስ
  • Bid Security60,000 (ስልሳ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO)
  • opening dateበዚሁ እለት ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት
  • Categories Furniture And Furnishing , Cleaning & Janitorial , Food And Beverage

Supply of office furniture, cleaning materials, vehicle and motor tires, construction materials, electronics, permanent office equipment, uniforms, catering services, food items, printing services and transportation services

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ -C-004/103/2018

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ - አላቂ የቢሮ እቃዎች የጽዳት እቃዎች ፤ የመኪናና የሞተር ጎማዎች ፣ የግንባታ እቃዎች ፣ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች ፤ ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፥ የደንብ ልብስ እቃዎች ፤ የግብዣ አገልግሎቶች የምግብ ግበዓቶች ፣ የህትመት አገልግሎትና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎችና አገልግሎቶች ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸዉን ያሳደሱና ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች በጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) 60,000 (ስልሳ ሺህ) ብር ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቹ የጨረታውን ሰነድ በአንድ ኮፒ ማዘጋጀትና እንዲሁም የጨረታውን ማስከበሪያ ሲፒኦ(CPO) በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) በጎባ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የሲንቄ ባንከ እካውንት ቁጥር 1071305601216 በማስገባት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15(አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-4 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ በ3፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዚሁ እለት ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-1 ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው የመከፈቻ ቀን በመንግሥት የሥራ ቀን የማይውል ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ::

ተጫረቾች የጨረታውን ሙሱ ይዘት (ገጽታ) ከጨረታ ሰነድ መረዳት ይችላሱ፡፡ ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር- 0913341620 / 0226611238

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የባሌ ዞን ጎባ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for supplying office furniture, cleaning materials, vehicle/motor tires, construction materials, electronics, permanent office equipment, uniforms, catering, food items, printing, and transportation services to government offices in Goba district. Bidders need valid trade licenses, tax clearance, and supplier registration.
Save Tender