Tender Detail

Tender Details

  • Company በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት
  • Address , Phone: 09 21 59 19 36
  • Website
  • Deadline23 Aug 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ (የማይመለስ)
  • Bid Securityበተረጋገጠ ሲፒኦ (ሎት1) 13,620 ብር (ሎት2) 10,455 ብር (ሎት3) 10,664 ብር (ሎት4) 1500 ብር (ሎት5) 50,000 ብር (ሎት6) 1000 ብር (ሎት7) 16000 ብር (ሎት8) 2000 ብር (ሎት9) 1500 ብር
  • opening dateጨረታው አየር ላይ ለተከታታይ 11 ቀን ቆይቶ በ11 ኛው ቀን 04፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

የተለያዩ እቃዎች ግዥ (የፅህፈት መስሪያ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የላብራቶሪ እቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ ህትመቶች፣ የዕድሳትና ጥገና ስራዎች፣ መስታንግዶ ከነ ሙሉ መብሳያ እቃ እና ጭነት)

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት የ2019 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- የፅህፈት መስሪያ እቃዎችና ሌሎች
  • ሎት 2፡- የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 3፡- የደንብ ልብሶች
  • ሎት 4፡- የላብራቶሪ እቃዎች የትምህርት መርጃ መሳሪያና መፅሐፍት
  • ሎት 5፡- የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 6፡- የተለያዩ ህትመቶች
  • ሎት 7፡- ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ ዕድሳትና ጥገና፡ ለህንፃ ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚ ዕድሳት እና ጥገና፡ ለመስረተልማት ዕድሳት እና ጥገና።
  • ሎት 8፡- መስታንግዶ ከነ ሙሉ መብሳያ እቃ
  • ሎት 9፡- ጭነት
  1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው የሰነድ ማስረጃዎችን ዋናውንና ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር በፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ እቃዎች በፎቶ እና ገዥው መ/ቤት ድርጅታችሁ በአካል መጥቶ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለበት።
  5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ጀሞ 2 ሸገር ማዞሪያ 200 ሜትር ገባ ብሎ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አከባቢ ከሚገኘው የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሎት1) 13,620 አስራ ሶስት ሺህ ስድስት መቶ ሃያ ብር (ሎት2) 10,455 አስር ሺህ አራት መቶ ሀምሳ አምስት ብር (ሎት3) 10,664 አስር ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ አራት ብር (ሎት4) 1500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር (ሎት5) 50,000 ሀምሳ ሺህ ብር (ሎት6) 1000 አንድ ሺህ ብር (ሎት7) 16000 አስራ ስድስት ሺህ ብር (ሎት8) 2000 ብር ሁለት ሺህ (ሎት9) 1500 አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀን 2፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ሰነድ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃዎች በሙሉ ጨረታ ከመከፈቱ ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ መሙላት አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 1% በባንክ /ሲፒኦ/ በተረጋገጠ ቼክ በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡበት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዢ ፈፃሚ አካል ማስያዝ አለባቸው። ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከወጡና ውሉ ተመላሽ ሲደርጉ ነው።
  11. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. እቃውን የሚያስገቡበት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት 7 እስከ 9 ሰዓት ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን። በተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እናሳውቃለን።

አድራሽ፡- በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቱ ልዩ ቦታው ጀሞ 2 ሸገር ማዞሪያ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ 200 ሜትር አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ

ስልክ ቁጥር 09 21 59 19 36 / 09 10 00 74 65 / 011 380 3469

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጋራ ፉሪ የመ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Procurement of various goods across 9 lots: office supplies, cleaning items, clothing, laboratory equipment, office furniture, electronics, printing, renovation/maintenance works, stationery, and transport. Bidders must hold valid licenses, pay taxes, be VAT-registered, and registered as suppliers with relevant authorities. Samples may be required.
Save Tender