Supply and Installation of Fruit sorting Processing and packing Machine
Source: World Bank — Second Agricultural Growth Project
የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የፍራፍሬ/አቦካዶ ማቀነባበሪያ ማሽን ግ»
በአማራ ብሔራዊ ክልዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ በግብርና እድገት ፕሮግራም በጀት ድጋፍ ለአትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት አገ/ት የሚውል የአቦካዶ ማቀነባበሪያ ማሽን አቅርበውና ገጽመው የሚያስረክቡ ህጋዊ የሆኑ አቅራቢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
በጨረታ ቁጥር ET-AAGP RPCU-224428-GO-RFB ለአትክልትና ፍራፍሬ ዳይሬክቶሬት አገ/ት የሚውል የፍራፍሬ/አቦካዶ ማቀነባበሪያ ማሽን አቅርቦና ገጥሞ ለማስረከብ የሚፈጸም ግዥ ዝርዝር መግለጫ
|
No |
Discription |
Specification |
Unit |
Amount |
Amount of BID Security ETB |
|
1 |
Supply and Installation of Fruit sorting /ABOCADO/ Processing and packing Machine |
As per attached on Biding Document |
set |
01 |
120,000 |
1. ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ለማቅረብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ / ስፔስፊኬሽን/ እንዲሁም የጨረታ መገምገሚያ ዘዴ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 67 በመምጣት የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር ማስያዝ አለባቸው፡፡
5.ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ጋር የቴክኒካል ፕሮፖዛሉን እና የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን ለየብቻ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በፖስታ በማሸግ በአብክመ ግብርና ቢሮ ቁጥር 012 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጠን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው እስከሚዘጋበት ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5.1 ተጫራቾች ከቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦሪጅናል ጋር አብሮ በፖስታ አሽገው ማቅረብ ያለባቸው ፤
-
-
- ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱት ማስረጃዎች በሙሉ፣
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በስንት ቀን ውስጥ እቃውን አጠቃሎ ገጥሞ ማስረከብ እንደሚችል የሚገልጽ ጽሑፍ እና
- የማቅረቢያ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናት ሲሆኑ እነዚህ መረጃዎች ጨረታው ሲከፈት ለቅድመ ማጣሪያ/ግምገማ የሚያገለግሉ ነጥቦች በመሆናቸው ተጫራቾች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የማቅረቢያ ቀኑን እና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀናትን ያልገለፀ ተጫራች መ/ቤቱ የገለፀውን የማቅረቢያ ቀን እና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን እንደተቀበለ ይቆጠራል፡፡
-
6. ጨረታው ሚያዚያ 11 ቀን 2013 ከቀኑ በ4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ በ4፡30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እነዚህ አካላት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 12 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 55 21 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 2266431 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ግብርና ቢሮ
