Tender Detail

Tender Details

  • Company የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ካፋ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 047 331 140
  • Website
  • Deadline12 Nov 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 500.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityሎት 1 ብር 100,000፤ ሎት 2 ብር 80,000 (CPO፣ ጥሬ ገንዘብ ወይም ቼክ)
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00
  • Categories Electronics Materials , Agricultural Products

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የችግኝ ጣቢያ ግብዓቶች ግዥ (2 ሎት፣ ግ/ጨ/ቁጥር 04/2017) - የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ /ግ/ጨ/ቁጥር 04/2017

የካፋ ዞን ፋይናንስና መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾች በመጋበዝ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል እስከ በጀት ዓመቱ ማብቂያ ማለትም እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ፡-
ሎት .1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ሎት .2. በካፋ ዞን ግብርና መምሪያ በጊምቦ ወረዳ ህብረት ቀበሌ ቡቂ -ኮሾ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኝ ጣቢያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግብዓቶች ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ ከገቢዎች ባለስልጣን የተሰጠ ክሊራንስ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ፣ የቫት ፣ የቲን ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ አያይዘ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክመንት ሲገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
  3. በመሆኑም ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸዉ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 / አምስት መቶ ብር/ካፋ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ቅ/ጽ/ቤት ቀርበው በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት ካፋ ዞን ፋይናንስ መመሪያ ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO (Certified payment order) ፣በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡ስለዚህ ለሎት .1. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ እና ለሎት .2ሎት በካፋ ዞን ግብርና መምሪያ በጊምቦ ወረዳ ህብረት ቀበሌ ቡቂ -ኮሾ የተለያዩ ግብዓቶች ግዥ 80,000.00 / ሰማኒያ ሺህ ብር/ ኦርጅናል ፋይናንሻል ሠነድ ጋር በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ቴክኒካል ዶክመንት የሚያስፈልገው ለሎት -1- ብቻ ነው፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሠነዱ ላይ በመጻፍ በሰም/በሙጫ/ በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም። 15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ የሚቆጠር ነው፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የዉል ማስከበሪያ /performance bond/ ለማስያዝ ፈቃደኛ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት ከላይ ሎት -1- እና ለሎት .2. የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ ካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አቅርቦ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ተጫራቾች አስሪዉ መ/ቤት ያዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያ/የቴክኒካል/ ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047 331 1826 በመደወል መጠየቅ ይቻላል!!

የካፋ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ቦንጋ

✨ messages.ai_summary
Kafa Zone Finance Department seeks bidders for two lots: various electronic items (Lot 1) and various inputs for a multi-purpose seedling station in Gimbo Woreda (Lot 2). Bidders must submit renewed business license, tax clearance, VAT/TIN and registration certificates, and supplier certificate. Technical document required for Lot 1 only.
Save Tender