የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የቢሮ እቃዎች፣ የሕትመት አገልግሎት እና የመስተንግዶ ግዢ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ/ካ/ገ/አስ/ፈ/ቤ/ት 001/2019
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ገዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የመንግሥት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በዘመኑ የታደሰ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ሎት፡- የጽሕፈት መሣሪያ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት2. የፅዳት ዕቃ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት3. የደንብ ልብስ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት4. ኤሌክትሮኒከስ፤ የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ/ ሎት5. ቋሚ የቢሮ እቃ 10,000/አስር ሺህ/ ሎት6. የሕትመት አገልግሎት 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት7. የመስተንግዶ ግዢ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ስም በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር የውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን (10%) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን ያስያዙት ሲፒኦ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ አቀራረቡ አንድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል አንድ ቴክኒካል ሰነድ ቅጂ፣ አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናል አንድ የፋይናንሻል ሰነድ ቅጂ፣ እንዲሁም ሲፒኦ እያንዳንዱ ለብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ መሆን አለበት፡፡ ፖስታው ላይ ኦርጅናል እና ቅጂ ምልክት በማድረግ እና የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከኢትዮ ሴራሚከስ ጎን በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል 16ኛ ፎቅ በመምጣት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 በተቋሙ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የመከፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ በኢ/ንግድ ባንክ በኢ/ካ/ገ/አ/ፍ/ቤት በተከፈተ አካውንት (1000670020308) ለእያንዳንዱ ሎት በማስገባት ከፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር በመረጡት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በማይቀደድና ጠንካራ መያዣ በማድረግ ለፋይናንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚቀርበው የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የንግድ ፈቃድና የአቅራቢነት ማስረጃ ኮፒ በግልጽ የሚታይ ይኖርበታል፡፡
- አቅራቢ ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት ንብረት ከፍል ማድረስ
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፦ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከኢትዮ ሴራሚክስ ጎን በሚገኘው ዋስትና የንግድ ማዕከል ሕንፃ 16ኛ ፎቅ
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ አስተዳደራዊ ፍርድ ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender No. ኢ/ካ/ገ/አስ/ፈ/ቤ/ት 001/2019, issued by the Ethiopian Capital Market Administrative Court, covers seven lots: office/stationery supplies, cleaning supplies, uniforms, electronic items, permanent office items, printing services, and hospitality purchases. Bid documents cost a non-refundable 200 ETB per lot. Bid security is a bank-confirmed CPO in the court's name: 5,000 ETB for stationery, cleaning, uniforms, and printing; 10,000 ETB for electronics and permanent office items; and 3,000 ETB for hospitality. Bids close on the 11th day at 4:00 PM and open at 4:30 PM the same day; bidders must hold a renewed trade license, business and VAT registration, government supplier registration, tax clearance, and submit item samples before opening.
