Tender Detail

Tender Details

  • Company በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa:Ethiopia, Phone: 0116663282
  • Website
  • Deadline20 Aug 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በየሎቱ
  • Bid SecurityCPO ማስያዣ; በየሎቱ የተለያየ መጠን (ለምሳሌ ሎት1 25,000 ብር)
  • opening dateበእለቱ 3:30
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

የቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ግዥ

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ጽ/ቤት


የ2019 ዓ.ም እንደኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን ሎት1 አላቂ እቃ /እስቴሽነሪ/ ሎት2 የጽዳት እቃ፣ ሎት3 የደንብ ልብስ፣ ሎት4 የኤሌክትሮኒከስ ሎት5 ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ፣ ሎት6 ህትመት ሎት7 መኪና ኪራይ፣ ሎት8 መስተንግዶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት/ ይፈልጋል፡፡

  1. በዚህም መሠረት በጨረታዉ ማሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች በዘፉ የታደሰ፥
  2. የንግድ ፈቃድ ምስከር ወረቀት
  3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት
  4. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት
  5. የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት የሚያቀርቡና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  6. ነጋዴዎች በነጋዴዎች ዌብሳይት ላይ ስም ዝርዝራቸው ለመኖሩ ፕሪንት እውት ማቅረብ አለባቸው::
  7. በሚያስገቡት ሰነድ ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም መምታትና መፈረም ስርዝ ድልዝ የተደረገ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቶች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር በየሎቱ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመከፈል የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. የሚያቀርቡት እቃ ዋጋ ከብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  10. በአነስተኛና ጥቃቅን የምትወዳደሩ ነጋዴዎች የምታስገቡት የድጋፍ ደብዳቤ ለሀገር ውስጥ ምርትና አምራችነታችሁን የሚገልጽ መሆን እንዳለበት እያሳወቅን፣ ከሀገር ውጪ ለሚመረቱ ለሚገቡ ምርቶች በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን
  11. በጨረታ ላይ ያጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦሪጅናል እና ጥራታቻውን የጠበቁ መሆን አለባቸው::
  12. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለሚያቀርቡት እታ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው የተወዳደሩበት እቃም በአስቶራቸው ውስጥ አስቶከ ያላቸው መሆን አለባቸው ከዚህ ውጪ እስቶክ በሌላቸው እቃ ተወዳድረው አሸናፊ መሆናቸውን ሲያውቁ ዋጋ ጨመረ በሚል ሰበብ እናቀርብም በሚሉ ነጋዴዎች ላይ ምከንያቱን የማንቀበል እና ቀጥታ ወደ ከስ የምንሄድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተ.ቁሎትየእቃው ዓይነትCPOየጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን
1ሎት 1አላቂ እቃCPO ማስያዣ25,00000
2ሎት 2የፅዳት ኢቃCPO ማስያዣ25,00000
3ሎት 3ደንብ ልብስCPO ማስያዣ25,00000
4ሎት 4ኤሌክትሮኒከስCPO ማስያዣ10,00000
5ሎት 5ህትመትCPO ማስያዣ600000
6ሎት 6ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይCPO ማስያዣ11,00000
7ሎት 7መስተንግዶCPO ማስያዣ15,00000
8ሎት 8ቋሚ እቃCPO ማስያዣ25,00000
9ሎት 9የትራንስፖርትCPO ማስያዣ11,00000
  1. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳው ድረስ ማምጣት አለባቸው::
  2. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን በመጨመር የቴክኒክና ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሁለት ፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በየካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን የሚያሲዙት በየሎቱ ሲሆን ለአንድ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ተ.ቁሎትየእቃው ዓይነትCPOየጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን
1ሎት 1አላቂ እቃCPO ማስያዣ25,00000
2ሎት 2የፅዳት ኢቃCPO ማስያዣ25,00000
3ሎት 3ደንብ ልብስCPO ማስያዣ25,00000
4ሎት 4ኤሌክትሮኒከስCPO ማስያዣ10,00000
5ሎት 5ህትመትCPO ማስያዣ600000
6ሎት 6ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይCPO ማስያዣ11,00000
7ሎት 7መስተንግዶCPO ማስያዣ15,00000
8ሎት 8ቋሚ እቃCPO ማስያዣ25,00000
9ሎት 9የትራንስፖርትCPO ማስያዣ11,00000
  1. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር በ15 ቀን ውስጥ የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፤ በመሆኑም 10% የውል ማስከበሪያ ያስገቡበትን ደረሰኝ ሳያወጡ እቃውን ብቻ የሚያመጡ ነጋዴዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።
  2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይሲሆን በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በእለቱ 3:30 የሚከፈት ሲሆን በጨረታው አከፋፈት ላይለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  3. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  4. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

እድራሻ፡-
መገናኛ ከዲያስፖራ አደባባይ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ ቶፕ ቪው አጠገብ የካ ተራራ ት/ቤት ፊት ለፊት ያለው የየካ ከ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
ለመረጃ ስልጥ ቁጥር 0911787170/ 0931503048/0910923695
በየካ ክ/ከተማ የወረዳ05 አስተዳደር ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
- Yeka Sub-city Woreda 05 Administration invites bids for office service items across multiple lots: stationery, cleaning supplies, uniforms, electronics, printing, decor and montarbo rental, hospitality, permanent items, and transport. - Bid documents cost a non-refundable 200 ETB per lot, available from the Woreda 05 Finance Office on the 2nd floor. - Bids close on the 11th working day from publication at 3:00 and open the same day at 3:30. - A CPO bid bond per lot is required, with amounts varying by lot (e.g., Lot 1: 25,000 ETB). Bidders must provide valid renewed trade license, tax clearance, business registration, VAT certificate when applicable, and proof of current tax payment; samples must be presented before opening. - Winners must provide a 10% contract performance guarantee and sign a contract within 15 days.
Save Tender