Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 ወደ ህዝብ ደህንነት እና አንቆርጫ መውጫ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0116677784
  • Website
  • Deadline20 Aug 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) የማይመለስ
  • Bid SecurityCPO በብር 10,000.00 (ለሎት 1 እና 2)፣ 10,000.00 (ለሎት 3)፣ 5,000.00 (ለሎት 4፣ 5 እና 6)
  • opening dateበዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather

የፅህፈት ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የኪራይ አገልግሎት እና የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ከ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎትየሚገዛው የዕቃ አይነትየጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በብርምርመራ
1የፅህፈት ዕቃዎች10,000.00
2የፅዳት ዕቃዎች10,000.00
3የደንብ ልብስ10000.00
4ህትመት5000.00
5የኪራይ አገልግሎት5000.00
6የመስተንግዶ አገልግሎት5000.00

በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ እና ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ ከገቢዎች የተሰጣቸውን ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000005067557 በየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስገባት እና የከፈላችሁበትን ኦርጅናል ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከየካ ከ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖለታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ማስረከብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከቀረበው ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዕቃ ዋጋ 10% CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡
  10. ክፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ በናሙና መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥ እና በንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን ብቻ ነው።
  11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ መግለጽ ወይም መሙላት አለባቸው።
  12. የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ካደራጃችሁ ተቋም ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 0116660974 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 ወደ ህዝብ ደህንነት እና አንቆርጫ መውጫ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Yeka Sub-city Woreda 10 Finance Office (Addis Ababa City Administration) invites bids under tender notice 01/2019 for six lots: office supplies, cleaning supplies, uniforms, printing, rental services, and hospitality services. Bid documents cost a non-refundable ETB 150.00 per lot; bid security (CPO) is ETB 10,000.00 for Lots 1–3 and ETB 5,000.00 for Lots 4–6. Submission closes on the 11th working day at 3:00 in the morning and opens the same day at 3:30; posted 2026-08-12. Bidders must hold a renewed business license, supplier registration, VAT/TIN registration, tax clearance, and must submit samples before opening; quoted prices must include VAT.
Save Tender