Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08፣ የቦታው ልዩ ስም ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115579512
  • Website
  • Deadline27 Aug 2018, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ
  • opening dateበዕለቱ ከቀኑ በ8፡30
  • Categories Building Materials , Other

የFiber Reinforced Fiberglass ተንቀሳቃሽ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ግዥ

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/G002/2018

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃና ፍሳሽ መሰረተ ልማት ማስፋፈያ ዲቪዥን ብዛት ሃምሳ (50) በFiber Reinforced Fiberglass የተሰሩ ተንቀሳቃሽ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት ልደታ በሚገኘው የህዝብ መናፈሻ ጎን ዲቪዥን ጽ/ቤት በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው እቃ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ።
  2. ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃ አቅራቢነት በፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ሰርትፍኬትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
  3. በጨረታው ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል። ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሰነድ ጋር በማስያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  4. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% (የውል ማስከበሪያ) ውል በተፈረመ በ15 ቀናት ውስጥ ማስያዝ ይኖርበታል። የሚገዙ እቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች መጠን 20% ሊጨምር ወይም 20% ሊቀንስ ይችላል።
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት። ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
  6. የጨረታ ሰነዱን በስሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
  7. ጨረታው ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 5ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል ። ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች ዲቪዥን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት መሰረት ግልጽ በሆነ መልኩ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል። የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት። ይህንን ያልገለጸ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
  9. ዲቪዥኑ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 08 የቦታው ልዩ ስም፡- ልደታ ኮንዶሚኒየም ልደታ መናፈሻ አጠገብ

ስልክ ቁጥር +251 11 5579036 (1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል)

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃና መሰረት ልማት ማስፋፊያ ዲቪዥን

✨ messages.ai_summary
- Procurement of 50 mobile public toilets made of Fiber Reinforced Fiberglass through national open tender (Tender No. AAWSA/WSIDD/GOV/NCB/G002/2018), issued by the Addis Ababa Water and Sewerage Authority, Water and Sanitation Infrastructure Development Division. - Bid documents are available for 300 ETB (non-refundable); a bid bond of 100,000 ETB via CPO, unconditional bank guarantee, or cash, valid for at least 90 days, is required. - Submission deadline is 8:00 AM on Nehasse 21, 2018 E.C.; bids are opened at 8:30 AM the same day at the 5th floor meeting hall. Posted on 2026-08-12. - Requirements include registration with the Ministry of Finance and Economic Development as a supplier, a renewed trade license, TIN and VAT registration certificates; prices must remain valid for 60 days, and a 10% contract performance security is due within 15 days of signing. Procured quantity may increase or decrease by 20%.
Save Tender