Tender Detail

Tender Details

  • Company አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር
  • Address , Phone: 0116376668
  • Website
  • Deadline18 Aug 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500.00 (አምስት መቶ ብር) (non-refundable)
  • Bid Securityለምድብ 1: 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 2 እና 3: 350,000.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና
  • opening dateከረፋዱ 5፡00 ሰአት
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Ict Equipment'S And Its Accessories

የቢሮ እቃዎች ግዥ (ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ፈርኒቸር)

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር AMFI 01/2019

  1. አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. ምድብ 1፦ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ
  3. ምድብ 2፦ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ
  4. ምድብ 3፡- የፈርኒቸር እና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፦

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምድብ 1 የሚቀርብ 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) እና ለምድብ 2 እና 3 የሚቀርብ ለእያንዳንዳቸው 350,000.00 (ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና በአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስም አሠርተው እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ አንድ ሰዓት) ድረስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ በአሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000505229014 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ለምድብ 1 ከጠዋቱ 3፡00 (ሦስት ሰዓት) ድረስ ለምድብ 2 ከቀኑ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ድረስ እና ለምድብ 3 ከቀኑ 8፡00 (ስምንት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ምድብ 1 ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ፣ ምድብ 2 ከረፋዱ 5፡00 ሰአት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 5፡30 ላይ እና ምድብ 3 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 8፡30 ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል፡፡ የመከፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
  6. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  8. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
  9. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦

በስልክ ቁጥር 011 637 66 68/011 637 64 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Akufada Microfinance Institution S.C. invites bids for the procurement of office items under three lots: Lot 1 – computers, printers and related items; Lot 2 – office equipment and related items; Lot 3 – furniture and related items. Bidders must hold a renewed trade license, tax identification certificate, VAT registration certificate, business registration certificate, current tax clearance certificate, and supplier registration certificate. Bid documents cost a non-refundable 500 ETB. Bid bonds are 400,000 ETB for Lot 1 and 350,000 ETB each for Lots 2 and 3, payable via CPO or bank guarantee. Submission is due on the 11th day after the announcement appears in the newspaper, with opening on the same day at specified times per lot.
Save Tender

Procurement of Office Equipment

READ MORE
በቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሎት-1 -ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት-2፡ - የፅዳት ዕቃዎች ፣ሎት-3 የደንብ ልብስ፣ሎት-4 የተሽከር...

READ MORE