የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ 2019 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣የጽዳት እቃዎችን፣የደንብ ልብሶችን፣ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ 2019 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣የጽዳት እቃዎችን፣የደንብ ልብሶችን፣ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 የደንብ ልብሶች
ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች
ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
ሎት 4 የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
በመሆኑም ተጫራቾች፤
1) በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብርከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስከር ወረቀት፣የአቅራቢነት የምስክርወረቀት፣ እና ለ 6 ወር ብቻ የሚያገለግል በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2) ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል።
3) ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል በሪጅን ጽ/ቤቱ 7ኛ ህንጻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል።
5) ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6) ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ይከፈታል። ክኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
7) ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን ዕቃዎች ጽ/ቤቱ ግምጃ ቤት 7ኛ ፎቅ ድረስ ማቅረብ
ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ ፡- ጅማ ከተማ አባ ጅፋር አደባባይ የጅማ ከተማ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት
አጠገብ ዋስትና ህንጻ ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ: 09 17 28 36 17 ወይም 09 17 87 80 57 መደወል ይቻላል።
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደርደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
ጅማ
