የአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ፤ፈርኒቸር፣የጽህፈት መሣሪያዎች፤የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት የአርሲ ዞን የዲግሉና ጢጆ ወ/ገ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019
የአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ፤ፈርኒቸር፣የጽህፈት መሣሪያዎች፤የጽዳት እቃዎች እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፤ በከልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒከስ እቃዎች፤ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ)፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸርእቃዎች እና ለጽዳት እቃዎች፤ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ) በአርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር1000061234253 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፣ ንብረት አስተዳደር፤ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ በዝግ ፖስታ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በዚሁ ዕለት ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ለጽህፈት መሣሪያዎች፤እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ)፤ ለ ፈርኒቸር እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) ፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንከ በከፍያ ማዘዣ(C.P.O.) ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ሳጉሬ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወራዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ሰ.ቁጥር 0222380790, 0910001453,0910758283, ይጠይቁ፡፡
አርሲ ዞን ዲገሉና ጢጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
