Tender Detail

Tender Details


የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ መስሪያ ቤቶች ግልጋሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር ጎማ እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ መስሪያ ቤቶች ግልጋሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ፣ ፈርኒቸር ፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና የተለያዩ የቢሮ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር ጎማ እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።  ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

1.    በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።

2.    ማንኛውም ተጫራች ንግድ ፍቃድ ከሚፈቅድለት ውጪ መወዳደር አይችልም።

3.    በአቅራቢነት መዝገብ መመዝገባቸውን ማቅረብ የሚችሉ።

4.    ማንኛውም ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

5.    የተጫራቾች ሙሉ ስም ፣ፊርማና የድርጅቱ ማህተም የሌለው እንዲሁም በዋጋ አጻጻፍ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።

6.    አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ የሚፈጸምላቸው ያሸነፉትን እቃዎች የአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት አጠናቀው ገቢ ካደረጉ በኋላ ነው፡፡

7.    ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ 20,000 (ሀያ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው።

8.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለያንዳንዱ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ከአርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ መውሰድ ትችላላችሁ።

9.    ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ከሞሉ በኋላ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 30/11/2018ዓ.ም 4፡00 ሰአት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ እንዲሁም በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አርሲ ሮቤ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በ4፡30 ሰአት በግልጽ ይከፈታል።

10.        አሸናፊ ተጫራች የፌዴራልና የክልሉን አዋጅና ደንቦችን የማክበርና በእቃ አቅራቢነት ወቅት የሚቀርበውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርበታል።

11.        አሸናፊ ተጫራች ከሚያቀርበው እቃ ጠቅላላ ዋጋ የሽያጭ ታክስ 3 ፐርሰንት ገቢ ያደርጋል።

12.        መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-09 13 86 50 03/ 09 28 03 57 25

 

በአርሲ ዞን የሮቤ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender