Tender Detail

Tender Details


በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በወረዳው አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጎማ፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ /ስፔር/ እና ጌጣጌጥ በመደበኛ በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2019

 

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሰንበቴ ከተማ ከአዲስ አበባ በደሴ ከተማ መስመር በ265 ኪ/ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ በ2019 በጀት አመት በወረዳው አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጎማ፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ /ስፔር/ እና ጌጣጌጥ በመደበኛ በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት

1.      በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በዘርፉ የተሠማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ንግድ ፈቃድ ፣ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /Tin no/ እና የVAT ተመዝጋቢ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት።

2.    በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ለተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከጅ/ጥ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 ከ 4/11/2018 እስከ 18/11/2018 መግዛት ይችላሉ። በጨረታው ሰነድ ላይ ዝርዝር ማብራሪያዎችን ያገኛሉ።

3.    ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ የአቅራቢው የባለቤት ስምና አድራሻ የሚገልፅ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት እስከ 19/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ጅ/ጥ/ወ/ገ/ፅ/ቤት ቢ.ቁ 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በዚሁ እለት 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል።

4.    ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት 19/11/2018 ዓ.ም 4፡30 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ይከፈታል።

5.    ጨረታውን በየእያንዳንዱ ሎት አይነት የምናወዳድር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

6.    ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለመኪና ጎማ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ /ስፔር/ እና ጌጣጌጥ 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ቢሮ ቁጥር 3 ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡

7.    መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው::

 

8.   ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0331180062/37 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ።

 

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጀ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender