Tender Detail

Tender Details

  • Company ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ አዋሽ ባንክ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 302 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +2519-61300180
  • Website
  • Deadline03 Jul 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ዘርፍ ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር)
  • opening date2026-07-03 10:30:00
  • Categories Accounting & Auditing

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር ለ2018 በጀት ዓመት የድርጅቱን የንብረትና የሀብት ግምት (Asset Valuation) ሥራ እና የ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብቱን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሠረት የውጭ ኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር (Waliif Education S.C.) የጨረታ ቁጥር፡ WE/AV/01/2018 (ለአሴት ቫሉዌሽን) እና WE/EA/02/2018 (ለውጭ ኦዲት)

ጨረታዉ የወጣበት ቀን፡ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር ለ2018 በጀት ዓመት የድርጅቱን የንብረትና የሀብት ግምት (Asset Valuation) ሥራ እና የ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብቱን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስታንዳርድ (IFRS) መሠረት የውጭ ኦዲት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1.     ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ የጋራ መሠረታዊ መስፈርቶች (Eligibility Criteria)

በየትኛውም ዘርፍ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን ህጋዊና ሙያዊ ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡-

•        በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት።

•        የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡ መሆናቸውን የሚያሳይ የግብር ማረጋገጫ (Tax Clearance Certificate)።

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)።

•        ተጫራቾች የቴክኒክ (Technical Proposal) እና የፋይናንስ (Financial Proposal) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ (Original እና Copy በማለት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

•        የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለእያንዳንዱ ዘርፍ ብር 10,000 (አሥር ሺህ ብር) በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም የማይሸረፍ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከቴክኒክ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2.     የየዘርፎቹ ልዩ የሥራ ዝርዝር እና ልዩ መስፈርቶች

ክፍል 1፡- የንብረትና የሀብት ግምት (Asset Valuation) ሥራ

•        የሥራው ዝርዝር (Scope of Work)፡- የአክሲዮን ማህበሩን ዋና መሥሪያ ቤት ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች (ለገጣፎ፣ ቢሾፍቱ፣ ገላን ጉዳ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ (3 ት/ቤቶች)፣ በደሌ፣ ቡል ሆራ፣ ሻኪሶ፣ ጂማ፣ እና ባሌ) የሚገኙ 12 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ይዞታዎች፣ ንብረቶችና ኢንቨስትመንቶች በ IFRS እና IVS መሠረት ሦስቱን ዋና ዋና የሀብት ክፍሎች (ቋሚ፣ የማይጨበጡ እና የፋይናንስ ኢንቨስትመንቶች) መገመት::

•        ልዩ የሙያ መስፈርት፡-

➢ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE) የተሰጠ እና በዘመኑ የታደሰ የአሴት ቫሉዌሽን ሥራ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት።

➢ የአክሲዮን ማህበራትን ወይም ተመሳሳይ ግዙፍ ተቋማትን የሶስቱንም የአሴት አይነቶች በጋራ (Combined) የመሥራት ቢያንስ የ3 (ሦስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ የተረጋገጠ የሥራ ልምድ ማስረጃ።

➢ ዋና ባለሙያዎች (Key Personnel) በAABE የተመዘገቡ፣ በIFRS እና IVS ዙሪያ በቂ እውቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።

ክፍል 2፡- የውጭ ኦዲት አገልግሎት ሥራ

•        የሥራው ዝርዝር (Scope of Work)፡- የማህበሩን የ2015፤ 2016 2017 እና 2018 በጀት ዓመታት የሂሳብ መዛግብት በ IFRS መሠረት ኦዲት ማድረግ፡፡ የፋይናንስ አሸናፊው የአራቱን ዓመታት (2015፣ 20161 2017 እና 2018) የኦዲት ሪፖርት በተስማማው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለይቶ ማጠናቀቅ አለበት።

•        ልዩ የሙያ መስፈርት፡-

➢ የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ወይም በAABE የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ።

➢ በAABE ዘንድ በ"Public Interest Entity (PIE)" ደረጃ የተመዘገቡ ወይም የአክሲዮን ማህበራትን ሂሳብ በ IFRS ለመመርመር ሙሉ ፍቃድ ያላቸው መሆን።

➢ የአክሲዮን ማህበራትን የ IFRS የውጭ ኦዲት ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ ያከናወነበትና ቢያንስ የ 5 (አምስት) ዓመት አጠቃላይ የኦዲት ልምድ።

➢ ለሥራው የሚሰማራው ቡድን በ IFRS ላይ በቂ እውቀትና ዓለም አቀፍ የሙያ ማረጋገጫ (እንደ ACCA, CPA ያሉ) ያላቸው መሆን እና ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ (Timeframe) ማቅረብ።

3.     የጨረታ ሰነድ መግዣ፣ መዝጊያና መክፈቻ ጊዜያት

➢ የሰነድ መግዣ፦ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ስዓት ከዋናው መሥሪያ ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

➢ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓት፡- በ10ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ፣ በዚያኑ ዕለት ከቀኑ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

•        (ማሳሰቢያ፡ ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል)።

ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ እና ስልክ ቁጥር

ዋሊፍ ኤዱኬሽን አክሲዮን ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት

አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 9፣ አዋሽ ባንክ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 302

ስልክ ቁጥር፡- +2519-61300180 / +251-913078297 / +251-10117426

ኢሜይል፡- nwesc25@gmail.com

 

Save Tender