Tender Detail

Tender Details

  • Company በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል
  • Address አዲስ አበባ ሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ /ገነት ሆቴል/ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0939500000
  • Website
  • Deadline07 Jul 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2026-07-07 14:30:00
  • Categories Textile, Garment & Leather

በኢትዮጵያ ኢንቨስትም ሆልድንግ ከሚተዳደሩት የመንግስት የልማት ድረጅት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለሆቴል የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የሰራተኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል


በድጋሚ የወጣ የሰራተኞች ደንብ

ልብስ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኢትዮጵያ ኢንቨስትም ሆልድንግ ከሚተዳደሩት የመንግስት የልማት ድረጅት ውስጥ ገነት ሆቴል አስተዳደር ለሆቴል የሰራተኞች የደንብ ልብስ እና የሰራተኛ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን ቅድመ ሆኔታዎች የምታሟሉ ተጫራጮች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

•        የ2018 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤

•        የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬት መለያ ቁጥር (TIN ሰነድ ያላቸው)

•        በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ፤

•        ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሀያ ሺህ ብር (20,000) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ “ለገነት ሆቴል” በሚል በማሰራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

•        ተጫራጮች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ለያንዳነዱ የጨረታ ሰነድ ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

•        ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት አለት ጀምሮ ባሉ አስራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ይሆናል።

•        መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ጨምሮ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ ለገነት ሆቴል አስተዳድር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል በአሰራ አምስተኛው ቀን አሰከ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል በአስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

•        ጨረታው ተጫራጮች ተወካዮች ባሉበት በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 በድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል።

•        አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም።

•        ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ በ0939500000 0911999072

 

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል

Save Tender