Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት
  • Address Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 033-431-88-20
  • Website
  • Deadline29 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineAdiss zemen
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2026-06-29 22:30:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Machinery , Electrical Materials , Office Equipment

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ስካነር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት


የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ወ/ሪጅ/ግጨ/004/2018
የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት

 Ethiopian Electric Utility


በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ስካነር፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 

የዕቃው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን

ሎት 1

አላቂ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች

92,437.00 /ዘጠና ሁለት ሽህ አራት መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ብቻ/

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡30


ሎት 2

የፕሪንተር ቀለሞች

24,545.60 (ሀያ አራት ሺ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር60/100)

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡30

ሎት-3

የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መጠቀሚያ ማሽኖች (ኮምፒዩተር ስካነርፕሪንተር ፎቶ ኮፒ እና ኤሌክትሮኒከስ…)

241,910.00/ሁልት መቶ አርባ አንድ ሺህ አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር ብቻ/

ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30

1.ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ እና ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin No/ ያላቸው

3. የመንግሥት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ እና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት በፖስታ አሽገው ሲመጡ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ እና ተያያዥ መረጃዎች የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት እና በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ወልዲያ ሪጅን ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ለሎት አንድ ብር92,437.00 /ዘጠና ሁለት ሽህ አራት መቶ ሠላሳ ሰባት ብር ብቻ/፣ ለሎት 2 ብር 24,545.60 (ሃያ አራት ሽህ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር ከ60/100 ብቻ )፣ ለሎት 3 241,910.00/ሁለት መቶ አርባ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መቅረብ አለበት፡፡

7. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ሳምፕል የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል “ኦሪጅናል እና ኮፒ እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በ4 በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ኢ/ኤ/አገ/ወ/ሪጅ/ግጨ/004/2018 የሚል ምልከት በማድረግ ለሎት 1 እና 2 ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለሎት 3 ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 15 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሎት 1 እና 2 ከጠዋቱ 4፡30 ለሎት 3 ከቀኑ 10፡30 ከሰዓት ላይይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልከ ቁጥር 033-431-88-20 መደወል ይችላሉ፡፡

12. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡


 
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ወልዲያ ሪጅን ኤ/አገ/ቤት ፅ/ቤት

Save Tender