የኖኅ መርከብ የበጎ አድራጎት ማኅበር የተባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ማኅበር ከሐምሌ 1, 2017 - ሰኔ 30, 2018 ዓም ያለውን ሒሳብ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
የኖኅ መርከብ የበጎ አድራጎት ማኅበር
የሒሳብ ምርመራ ጨረታ
የኖኅ መርከብ የበጎ አድራጎት ማኅበር የተባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ማኅበር ከሐምሌ 1, 2017 - ሰኔ 30, 2018 ዓም ያለውን ሒሳብ የኦዲት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ በዚህ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው
3. የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ያላቸው
4. ከኢትዮጵያ የሒሳብና ኦዲት ቦርድ የሙያ ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
5. በIPSAS የሒሳብ አያያዝ መሰረት ኦዲት ማድረግ የሚችሉ
6. የጨረታው ሰነድ፤ ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚወስደውን ጊዜና የአገልግሎት ዋጋ ከፍያ በታሸገ ፖስታ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በአዲስ አበባ፤ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፤ ወረዳ 09 የቤት ቁጥር 733 በሚገኘው የድርጅታችን ቢሮ ድረስ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሶስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
8. ለተጨማሪ መረጃ የስልክ ቁጥር 0911698498 ወይም 0911405053 በመደወል ማግኘት ይቻላል::
የኖኅ መርከብ የበጎ አድራጎት ማኅበር
