ቪዥን አፍሪካ አካዳሚ አክሲዮን ማህበር ከ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 በጀት ዓመታት የሂሳብ መግለጫ የሚያቀርቡ የውጪ ኦዲተሮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ቪዥን አፍሪካ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበር
የጨረታ ማስታወቂያ
ቪዥን አፍሪካ አካዳሚ አክሲዮን ማህበር ከ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 በጀት ዓመታት የሂሳብ መግለጫ የሚያቀርቡ የውጪ ኦዲተሮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ግራር ኮንዶሚኒየም ከፍ ብሎ የሚገኝ ቪዥን አፍሪካ አካዳሚ አከሲዮን ማህበር ቢሮ አስፈላጊ ማስረጃዎችን ኦርጅናል እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በሥራ ሰዓት መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ግዴታዎች፡-
1. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
2. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
3. በቂ የሥራ ልምድ ያለው
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
5. ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርቱን ለጠቅላላ ጉባኤ አቅርቦ የሚያፀድቅ እና ሥራውን ሠርቶ ለመጨረስ የሚፈጅበትን ጊዜ እና ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚሠራበት የአገልግሎት ዋጋ የሚያቀርብ መሆን ይኖበታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913 39 65 93 / 0929 83 41 49 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ቪዥን አፍሪካ አካዳሚ አክሲዮን ማኅበር
