Tender Detail

Tender Details

  • Company አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
  • Address Ambo Ethiopia, Phone: 0112609101
  • Website
  • Deadline25 Jun 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Securityበቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • opening date2026-06-26 11:00:00
  • Categories Food Items And Drinks

የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ. የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2,774 ± ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 = ኩንታል ቀይ ጤፍ 517: በጠቅላላው 4,641 ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ


ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ. የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2,774 ± ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 = ኩንታል ቀይ ጤፍ 517: በጠቅላላው 4,641 ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው ነገሮች

1.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩኒየኑ ገበያ መምሪያ በብር 1000.00 መግዛት ይችላሉ፡

2.     የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፤፤

3.     ተጫራቾች እህሎቹ ያሉበትን ሁኔታ አምቦ ከተማ በሚገኛው የዩኒየኑ መጋዘን በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ወዲያው የሚመለስላቸው ይሆናል፡፡

5.     ጨረታው ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ17ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ 5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 17ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥላው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤፤

6.     ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ በሰዓቱ ይከፈታል፡፡

7.     ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ ጨረታውን በአንዱ የእህል ዓይነት ወይም በሁሉም የእህል ዓይነት ላይ መጫረት ይችላል፡፡

9.     ጨረታውን ያሸናፈ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላለውን ግዥ ዋጋ ባስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ላይ 5% ለዋስትና በባንክ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤፤

10.                        ዩኒየኑ ለእህሉ ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ስበስm መረጃ ስልክ ቁጥር 0112609101 ወደም 0112363399 ይጠቀሙ።

 

አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ

Save Tender