Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Address በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋ ሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምዕራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 20 20 56 42
  • Website
  • Deadline16 Jun 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security10,000 /አስር ሺህ ብር/
  • opening date2026-06-16 10:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Transportation Service And Cargo

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ 01/2019

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት ከሃምሌ 01/2018 እስከ ሰኔ 30/2019 ድረስ የሚቆይ የተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም:-

•        ሎት 1. የጽዳት አገልግሎት /Out source/

•        ሎት 2. የሰራተኞች የትራንስፖርት ሰርቢስ አገልግሎት

•        ሎት 3. የደረቅ ጭነት አገልግሎት

•        ሎት 4. የመኪና ጥገና አገልግሎት

•        ሎት 5. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /tin /ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3.     የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4.     የጨረታ ሰነዱን በብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሆስፒታሉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስ/ሒደት ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡

5.     የጨረታ ማስከበሪያ ያስገቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ያከሉን ለሆስፒታሉ በCPO/ በመሂ1 ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።

6.     ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ለሚገዙ አገልግሎቶች 3% የመቁረጥ እና በሥማቸው የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ አለባቸው።

7.     አሸናፊ ሆኖ የሚገባው ተጫራች የፅዳት አገልግሎቱን ለ 24፡00 ሰዓት ሳይቆራረጥ መስጠት አለበት። በመሆኑም የፅዳት ቋሚና አላቂ ግብአቶች በወሩ መጀመሪያ 1–3 ባሉት ቀናት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡

8.     የሰራተኛ ሰርቢሱ 28 ወንበርና ከዚያ በላይ ያለው ደረጃ አንድ ቅጥቅጥ መሆን አለበት ፡፡

9.     የተሸከርካሪው የስምሪት ዘመን/የምርት ዘመን እ.አ.አ ከ2013 ወዲህ የተመረተ /አዲስ ሞዴል መሆን አለበት፡፡

10. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ለመኪናው የሚያስፈልጉ የተለያዩ ወጪዎች እና የናፍታ ከፍያ በራሱ በተጫራቹ ነው፡፡

11. ተሸከርካሪው ሙሉ ቀን ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚሠጥ/መስጠት/ የሚችል መሆን አለበት ፡፡

12. የተሸከርካሪው ሊብሬ በተጫራቹ ስም የሆነ ኢንሹራንስ እና ሶስተኛ ወገን የተገባለት እንዲሁም የቴከኒክ ምርመራ/ቦሎ/ ያሰራ መሆን አለበት፡፡

13. ተሸከርካሪው በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት፡፡

14. ለሁሉም ሎቶች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ሥማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡

15. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበሪያ 10% ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በ C.P.O በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡

16. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ዝርዝር አባሪ ዶክመንቶችን ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

17. ጨረታው ከፍት ሆኖ የሚቆየው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡

18. ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ እና ሠዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት በሆስፒታሉ በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቻው) በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡

19. ለሁሉም ሎቶች ተጨማሪ መረጃዎችን ከጨረታው መመሪያና ከዋጋው መሙሊያ ላይ ማግኘት ይቻላል።

20. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የሥራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ በቀጣዩ ባለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡

21. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

22. ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 09 20 20 56 42 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

አድራሻ፡- በደሴ መስመር በሚወስደው አስፋልት ከሸዋሮቢት ከተማ 3 ኪሎ ሜትር አለፍ ብሎ ወደ ምእራብ 500 ሜትር ገባ ብሎ እንገኛለን፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

Save Tender