Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ለ2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።


የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ፣ ጨረታ ቁጥር ////06/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች 2018 በጀት ዓመት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡-

·        ሎት 1- አላቂ የህምና አቅርቦቶች ግዥ

·        ሎት 2- የኦክስጅን አቅርቦት ግዥ

·        ሎት 3፡- የምግብ አቅርቦት ግዥ

·        ሎት 4፡- የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ተጫራች፡-

1.     በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ፍቃዱን ያደሰ፤

2.     የተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ ወይም የሙያ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለውና፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3.     የአቅራቢነት ማስረጃ ያለው፤

4.     ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ስለ ግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሣተፍ የጨረታ ማስከበሪያ

·        ሎት 1- አላቂ የህምና አቅርቦቶች ግዥ 50,000.00 ብር

·        ሎት 2- የኦክስጅን አቅርቦት ግዥ 100,000.00 ብር

·        ሎት 3፡- የምግብ አቅርቦት ግዥ 100,000.00 ብር

·        ሎት 4- የአጥንት ምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ 350,000.00 ብር

በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

6.     ተጫራቾች የናሙናዎቻቸውን ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮዳቸውን ሰጥተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ለአንድ የአቅርቦት ዓይነት አንድ ናሙና ብቻ ማቅረብ አለባቸው፡፡ (ለምግብ አቅርቦት)

7.     አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የእቃ ምችት (የራሱ ስቶክ) ያለውና፤ እቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ (ወጪ) እስከ ሆስፒታሉ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ አምጥቶ እና በራሱ ወጪ አውርዶ ማስረከብ አለበት

8.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ መረጃቸውን እና፤ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት መምጣት ይኖርባቸዋል፤ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋት 230 እስከ 1000 ሰዓት በሆስፒታሉ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አዲስ (በመኪና መግቢያ በር ገብቶ ወደ ግራ እጥፍ ብለው) በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

9.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ የሎት ቁጥሩ፤ ሰነድ ሲገዙ የተሰጣቸው መለያ ኮድ ፅፈው፣ የድርጅታቸው ህጋዊ ማህተም መተው፤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ያሉት ጨረታቸው አንድ (1) ኤንቨሎፕ ነው፡፡ እንዲሁም ሎት 4 የአጥንት ህክምና መሣሪያ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ ጨረታቸው ሁለት (2) ኤንቨሎፕ ሲሆን (ሎት 4 በአራት ፖስታ በሁለት አርጅናል እና ሁለት ኮፒ) ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ለየብቻ አሽገው፤ ኦርጅናል እና ኮፒ ለይተው ማስገባት ይኖርባችኋል

10. ጨረታው 10 ቀናት የአየር ላይ ቆይታውን እንዳጠናቀቀ 11ኛው ቀን ጠዋት 300 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ጠዋት 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸው ሆስፒታላችን በሰጠው መሙያ ቅጽ ብቻ መሙላት ይኖርባችኋል፤ ማንኛውም ስርዝ ድልዝ፣ ማህተም ያልተደረገበት የቀረበ ዋጋ፣ በሆስፒታሉ ዋጋ መሙያ ቅጽ ያልተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡ ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡

12. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው

 

አድራሻ፡- በአራዳ ጊዮርጊስ / ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ከዮሐንስ / 500 ሜትር እንገኛን፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ

በስልክ ቁጥር 0111112056 ደው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የራስ ደስታ ዳምጠው ሆስፒታል

Save Tender

ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የወጣ የተለያዩ ዕቃዎችን ግዢ ለመፈፀም የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 0023/2019

READ MORE