የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2018 በጀት የካምፓኒውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጪ አዲተር አዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2018 በጀት የካምፓኒውን የፋይናንስ እንቅስቃሴ በውጪ አዲተር አዲት ማስደረግ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ የአዲት ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል፡፡
1. በአዲት ስራ ፈቃድ ያለው እና የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያለው፣ እንዲሁም የንግድ ሥራ ፈቃዱን በዘመኑ የታደሰ፣
2. የቲን ነምበር፣ የቫት እና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
4. የአዲት ስራው የሚከናወነው በ IFRS እና በ GAAP የሪፖርት አሰራር መሰረት መሆን አለበት፡፡
5. የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፤
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ በድርጅታችን ስም ማስያዝ አለባቸው።
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
8. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች አሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን/ ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቶች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
11. የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. ተጫራቹ የአገልግሎት ዋጋውን ሲሞላ ለሚያሰማራቸው ባለሙያዎች የትራንስፖርት፣ አበልና የተለያዩ የመስተንግዶ ወጪዎችን ታሳቢ አድርጐ መሙላት አለበት፡፡
13. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፣
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
15. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 36 84 37/09 10 19 31 73 ደውለው ይጠይቁ።
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
