ኩባንያችን ለዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
Tsehay Insurance S.C.
ፀሐይኢንሹራንስ አ.ማ.
የጨረታ ማስታወቂያ (Ref No. TISC/ HRPA/017/2026)
ኩባንያችን ለዋና መ/ቤት ህንፃ ግንባታ ሲጠቀምበት የነበረውን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን) ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ለመሸጥ የተዘጋጁትን ቁርጥራጭ እንጨቶች እና ፕላይዉድ (ሳፋሪያን)ፒያሳ አዲስ አበባ ሬስቶራንት ፊት ለፊት በሚገኘው የኩባንያው ህንፃ ከግንቦት 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካል በመገኘት እና በማየት የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 25/09/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የቀድሞው ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ዋና መ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ በማድረግ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቦሌ ከሚገኘው የኩባንያው ዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በአካል በመገኘት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በሌሎች ተጫራቾች በተሰጠ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) 15% በተጨማሪነት ይከፍላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ውጤት ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመፈፀም ንብረቱን ከቦታው ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ያስያዙት CPO ለኩባንያው ገቢ ይደረጋል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111119771/70/0968580008 በመደወል ወይም ከላይ በተጠቀሰው ዋና መ/ቤት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ
