አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው ግሎባል ኢትዮጵያ የሴቶች ማህበር የ2017 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ማሠራት ይፈልጋል።
ግሎባል ኢትዮጵያ የሴቶች ማህበር
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነው ግሎባል ኢትዮጵያ የሴቶች ማህበር የ2017 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ማሠራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ
1. የድርጅታችሁን እንቅስቃሴ የሚገልጽ መረጃ (Profile)
2. 2018 ዓ.ም የታደሰ የሥራ ፈቃድ
3. ከፌደራል ኦዲተር ጀኔራል የተሰጠ የሙያ ፈቃድ
4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) እና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሚቀጥት 5 /አምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ስድስት ኪሎ ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ሦስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303A በሚገኘው ቢሯችን በሰም በታሸገ ጨረታችሁን እንድታቀርቡ በአክብሮት ይጋብዛል።
ግሎባል ኢትዮጵያ የሴቶች ማህበር
