Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Bank of Ethiopia
  • Address P. O. Box 255, Addis Ababa, Ethiopia, Tel. 251-11-372-28-72, 251-11-372-28-26., Phone: 251-11-372-28-72
  • Website
  • Deadline02 Jun 2026, 2:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-06-02 03:00:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia


የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 

 

  ተ.ቁ

የተበዳሪው ስም የንብረት

 አስያዥ

ስም

የመያዣ ንብረቱ መለያ የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር) ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት
የሰሌዳ ቁጥር ሞተር ቁጥር የሻንሲ ቁጥር የንብረቱ አይነት የሥሪት ዘመን
1. ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ወንድም ፈለቀ አአ-02- C33705 G4LANM147995 MALB241C8NM149028 ሃዩንዳይ ግራንድ i10 አዉቶሞቢል 2022 3,098,304.00 25/09/2018 ዓ.ም

3፡00-4፡00 ጠዋት

2. አቶ ናስር ካሊል ሞሐመድ ተበዳሪው 02-AA-B76699 JFC92432. 1FTEX1EP1JFC92432 ፎርድ F150 ኪንግ ካፕ 2018 4,765,200.00 25/09/2018 ዓ.ም

4፡00-5፡00 ጠዋት

3. ወ/ሮ ዉዳሴ አበበ ቸኮል ቴዎድሮስ አበበ ቸኮል AA-02-B52539 FEAJ11.HRA*696746A* SJNFEAJ11UL2399086 አዉቶሞብል 2018 2,673,000.00 25/09/2018 ዓ.ም

5፡00-6፡00 ጠዋት

4. ኳድራንት አፓርል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ተበዳሪው ኢት-03-66900       እና

ኢት-03-20264

F3BEE681G*B220222647* WjME3TRE8EC286633

እና  TT-1044-14

የጭነት እና ተሳቢ ተሽከርካሪ 2014 11,033,376.00 25/09/2018 ዓ.ም

8፡00-9፡00 ከሰዓት

 

በመሆኑም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው፡፡
  2. ጨረታዉ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነዉ፡፡
  3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል፡፡
  4. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡
  6. ንብረቱን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል፡፡
  7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ንብረቱን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም፡፡ ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን ካልተረከበ ከንብረቱ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
  9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው

ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል፡፡

 

Save Tender