Tender Detail

Tender Details

  • Company Defense Construction Design Enterprise
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline22 May 2026, 10:00 AM
  • magazineReporter Tenders
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-05-22 10:30:00
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Defense Construction Design Enterprise


የጨረታ ማስታወቂያ

  ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር DCDE 010/2018

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት የሚኙትን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይቻላል፡፡

  1. ተጫራቾች የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ፋይናንስ ዴስክ በመምጣት የተሸከርካሪዎች ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው ከግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ከግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ ግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ባሉት የስራ ቀናቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ተሸከርካሪዎቹን በአካል ማየት የሚችሉ ሲሆን ተሸከርካሪዎቹን ለማየት ሲመጡ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ከግንቦት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ አስተዳደርና ፋይናንስ ቡድን 4ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉለውም፡፡
  4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ መነሻ 20 በመቶ (20%) በመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት (Defence Construction Design Enterprise) ስም የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ብቻ ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመታሸጉ በፊት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሲፒኦ(CPO) የተሰራው ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች የግምገማው ውጤት ለተጫራቾች ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ20 የስራ ቀናቶች ውስጥ ሲፒኦ(CPO) ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  6. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተወዳዳሪ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
  9. በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ብቻ በመሆናቸው የኢትዮጵያ የመገበያያ ገንዘብ በሻጭ እና በገዥ መካከል ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 896 06 33/011 896 06 23

አድራሻ ካሳንቺስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጀርባ ከዚህ ቀደም ስኳር ኮርፖሬሽን የነበረበት የኪያ-ሜድ ኮሌጅ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ

Save Tender