የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኤሌክትሪክ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
010-2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ኤሌክትሪክ ሚኒባስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የሚገዛው የአገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (cpo) |
ምርመራ |
|
1 |
የመኪና ኪራይ |
10,000.00 |
|
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ቲን /Tim/ ሰርተፊኬት እና ክሊራንስ ማስረጃ እንዲሁም ሶስተኛ ወገን፣ ቦሎ እና ኢንሹራንስ የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ተሽከርካሪ ጥራትና ቁመና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጡ መስፈርቶች መሰረት ተቋማችን በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት የፋይናንስ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት አቅርበው በጥራት ኮሚቴ ቴክኒክ ምርመራ የሚካሄድ ይሆናል፤
3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ ህንጻ 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10-04 ከፋ-ይናንስ ዳይሬክቶሬት ክፍል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት 10ኛ ፎቅ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10-08 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለውድድር የሚቀርበው የቴክኒከ ሰነድ እንዲሁም የዋጋ ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒ በተሊያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ጨረታው በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ለም ሆቴል አካባቢ ኤም ኤ 10ኛ ፎቅ እንገኛለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0911002020/ 0913727549
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ
