Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ስነ-ሕይወት ባለሙያዎች ማህበር
  • Address የተፈጥሮና ኮምፒቲሽናል ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0921398625
  • Website
  • Deadline22 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-22 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ ሥነ ሕይወት ባለሞያዎች ማህበር የ2025 በጀት ዓመት ሂሳቡን በውጪ ኦዲተሮች ማሰራት ይፈልጋል።

የኢትዮጵያ ስነ-ሕይወት ባለሙያዎች ማህበር


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ ሥነ ሕይወት ባለሞያዎች ማህበር የ2025 በጀት ዓመት ሂሳቡን በውጪ ኦዲተሮች ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን ይህንኑ የሚያስረዳ ማስረጃ ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ ሥራውን መጀመር የሚችሉ ሲሆን ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚወስድባቸው ጊዜ በመግለፅ የሚሰሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የቀረበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ የሂሳብ ባለሞያ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት /10/ አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ጨረታውን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 

አድራሻ፡- የተፈጥሮና ኮምፒቲሽናል ሳይንስ ኮሌጅ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

ስልክ ቁጥር፡- 0921398625

ኢሜይል፡- biologicalsocietyec@gmail.com

 

የኢትዮጵያ ሥነ ሕይወት ባለሞያዎች ማህበር

Save Tender