የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/Dis/02/2018(NCB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክት ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት ያገለገሉ ትራንስፎርመሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች -
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሰ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
2. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ሕንፃ 11ኛ ፎቅ በመቅረብ የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guaran-tee) በኢ ኤ.አ ፕሮጀክት ፖርትፖልዮ ማኔጅመንት ወይም EELU-PPM ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-PPM/Dis/02/2018 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክቶች ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ዋስትና የንግድ ማዕከል ሕንፃ 11ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ነው በመቅረብ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
4. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ዕቃዎች በሚገኙበት ዕቃ ግምጃ ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
6. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፋችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለውድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ 8:30 ይከፈታል፣
8. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ይመልከቱ።
9. የፕሮግራም ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111275503 መደወል ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ ማኔጅመንት ጽ/ቤት
