የደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በ2018 የበጀት ዘመን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን ግዥዎች በሎት 1 የቢሮ ፈርኒቸር፣ በሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሚዛን አማን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በ2018 የበጀት ዘመን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ያላቸውን ግዥዎች በሎት 1 የቢሮ ፈርኒቸር፣ በሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከአቅራቢዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች የተሰማሩበት የሥራ ዘርፋ የሚገልጽ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይ የመለያ ቁጥር ያለው።
3. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል፡፡
4. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችል፡፡
5. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ cpo፤ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ እና በካሽ ማቅረብ የሚችል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ከክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 003 የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል አንድ ላይ በማሸግ በፖስታ በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ንብረት በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ንብረት ክፍል ገቢማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
9. አሸናፊ የሆነበት የቢሮ ፈርኒቸሮች ገጥሞ በባለሙያ ሲረጋገጥ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል።
10. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ሕጋዊ ወኪል ፊርማ፤ የድርጅቱ ማህተም እንዲሁም አድራሻ እና ስልከ ቁጥር በመግለጽ መጻፍ አለበት፡፡
11. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን በክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በዛው ቀን 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
12. ሆኖም ግን ጨረታው የሚታሸግበት ሆነ የሚከፈትበት ቀን ከመንግሥት የሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0471356632
የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሚዛን አማን
