Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ስ/ጤ/ጣ/002/2018

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተገለፁትን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች፣ መድሃኒቶች የህክምና መሳሪያዎች፣ ቋሚ እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ የቫት ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለባቸው

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን እና የታደሰ መሆን አለበት እንዲሁም ከግዥ ኤጀንሲ online ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማስያዝ አለባቸው።

3.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበት እቃ ናሙና በእስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል እና ለቋሚ እቃ ፎቶ ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም በእጃቸው ላይ የሚገኝ በተጠየቁ ሰዓት ወዲያው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን በባንክ በተረጋገጠ የኢትየጵያ ንግድ ባንከ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ አለባቸው፡፡

5.     በጨረታ ሰነዱላይ የተገለፀው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የጨረታው መመሪያ ሆኖ ችግሮች ካጋጠሙ በግዥው መመሪያ የሚዳኙ ይሆናል፡፡

6.     ተጫራቾች የሞሉትን ሰነድ በፖስታ አሽገው ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ብለው በመፃፍ የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7.     የውል ማስከበሪያ የግዥውን ግምታዊ ዋጋ 10% ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

8.     የወሰዱትን ሰነድ ዋናዋና ቦታዎች ላይ እና ዋጋ የሞሉበት ሰነድ በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም በመምታት ሙሉ ሰነዱን ተመላሽ ማድረግ አለባቸው።

9.     መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየርላይ በዋለ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 412 ይከፈታል፡፡

11. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው አስር የስራ ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 412 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነድ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

12. የላብራቶሬ ሬኤጅንቶች ላይ የምትወዳደሩ የFDA (ከኢትዮጵያ ከመዳኒት አቅራቢ ድርጀት የፍቃድ ሰርተፍኬት ማያያዝ አለበችሁ

13. ከጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾች ከተቋሙ በፅ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እና ስለሚያመርቱት ምርት ሰርተፍኬት ማምጣት አለባቸው፡፡

14. የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ወይም በካሽ መቅረብ ስላለበት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ እንድታሲዙ እያሳሰብን ለጨረታ ማስከበሪያ የምታቀርቡት (የምታሰሩት) (CPO) ወይም በካሽ ብቻ ማስያዝ እንዳለባችሁ እና የምታስይዙትን በየሎቱ በዝርዝር እንደሚከተለው አስቀምጠናል፡፡

 

በመሆኑም

•        6214 - የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች ላይ የሚወዳደር = 60,000.00 ብር

•        6313 - ቋሚ እቃ ላይ የሚወዳደር = 20,000.00 ብር

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በወረዳ 8 ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር /011-439-89-08 ይደውሉ

ከአንድ በላይ ጨረታ የወጡ መደቦች ላይ ዋጋ የሚሞላ ተጫራች የሞላውን እቃ ድምር ሁሉም ላይ የሞላ ደግሞ የሁሉንም ድምር የጨረታ ማስከበሪያ ማሳያዝ አለበት፡፡

 

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ሰርጢ ጤና ጣቢያ

Save Tender