Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ
  • Address ልደታ ክ/ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-273-43-49
  • Website
  • Deadline15 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • opening date2026-04-15 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Office Supplies And Services , Used Items

በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡ 01/2018

 

በልደታ /ከተማ ጤና /ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ 2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ ካደራጃቸው ተቋም ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት አንስቶ በአብነት ጤና ጣቢያ ፎቅ የግዥ ፍል በመምጣት ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 230 እስከ 1100 ሰዓት) የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

3.     ተጫራቾች ለሚገዙት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ።

4.     በጨረታው ለመካፈል ሰነድ የገዙ ድርጅቶች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 230 እስከ 1030 ሰዓት) በአብነት ጤና ጣቢያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ በማሳየት እቃዎቹን መመልከት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን በታሸገ ኢንቪሎፕ ማስታወቂያዉ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአብነት ጤና ጣቢያ 1 ፎቅ የግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪቻቸዉ በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 300 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 330 ሰዓት በአብነት ጤና ጣቢያ አደራሽ ይከፈታል። የመፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

7.     በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው አምስት የስራ ቀናት ውስጥ የእቃዎቹን ሙሉ ክፍያ መክፈል ይጠበቅባቸዋል።

8.     በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት የእቃውን ሙሉ ክፍያ ከከፈለበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎቹን የማንሳት ግዴታ አለበት። አሸናፊው ተጫራች በተጠቀሰው ጊዜ ገድብ ውስጥ እቃዎቹን ማንሳት ካልቻለ በየቀኑ 500 (አምስት መቶ ብር) እየጨመረ የሚሄድና 5 ቀናት በኋላ ንብረቱ የሚወረስ መሆኑ እንዲሁም ማስያዣ የተያዘው ገንዘብ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንደሚደረግ፤

9.     መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ

በስልክ ቁጥር፡- 011-273-43-49/39/59

አድራሻ፡- ልደታ /ከተማ አብነት ጤና ጣቢያ ከአብነት አደባባይ ፊት ለፊት ግቤ ህንፃ ጎን 100 ሜትር ገባ ብሎ

 

በልደታ /ከተማ ጤና /ቤት የአብነት ጤና ጣቢያ

Save Tender