በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት ለአካዳሚው ሠልጣኞች በተዘጋጀ ሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን አዘጋጅቶ ማቅረብና መመገብ የሚችሉ ድርጅቶችን ወይም ማኅበራትን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሠረት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመመገብ ይፈልጋል።
በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግሥት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ለ2018 በጀት ዓመት ለአካዳሚው ሠልጣኞች በተዘጋጀ ሜኑ መሠረት የተለያዩ የምግብ አይነቶችን አዘጋጅቶ ማቅረብና መመገብ የሚችሉ ድርጅቶችን ወይም ማኅበራትን ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሠረት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመመገብ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመጫረቻ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1. በዘርፉ የተመዘገበ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ እና የዘመኑ ግብር የከፈለበትን መረጃ ማቅረብ የሚችል
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin number) ማቅረብ የሚችል
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ የሆነ
5. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት ማቅረብ የሚችል፤
6. ከክፍያው 3% ተቀናሽ የቅድመ ግብር /withholding/ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታውን ተወዳድሮ ሲያሸንፍ የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ቢያንስ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሌተር ኦፍ ክሬዲት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች መገምገሚያ ሠነዱን መ/ቤቱ በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት ተፈርሞበት እና በእያንዳንዱ ሠነድ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ መቀመጥ አለበት፡፡
9. የጨረታ ሰነዱ ሁለት /2/ ፖስታ ማለትም በኦርጅናል እና በኮፒ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ በመቅረብ ከፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር3 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
10. ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ ይዘው ሲያቀርቡ የቴክኒካል እና የፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻ በማድረግ የተለያዩ ሁለት [2] ፖስታ በሰም በታሸገ በኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
11. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16 ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
12. ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ማሸነፉ በተገለፀለት በ7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል በመግባት ለአካዳሚው ሰልጣኞች በሜኑ መሰረት የተለያዩ የምግብ አይነቶች በማዘጋጀት በሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ አማን ግቢ ውስጥ ለሠልጣኞች የምገባ ሥራ መጀመር አለበት፡፡ ይህ ባይሆን ግን ለጨረታው እና ውል ማስከበሪያ ተብሎ ያስያዘው /CPO/ ውርስ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ሚዛን-አማን
በደቡብ ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የሚዛን አማን ስፖርት አካዳሚ
