በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለንብ ቀፎ መስሪያ የሚያገለግሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸውን ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ሥራና ክህሎት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለንብ ቀፎ መስሪያ የሚያገለግሉ የተለያየ ሳይዝ ያላቸውን ጣውላዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፣
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ በግብር ከፋይነት የተመዘገበ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታውን የተወጣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉበት የጊዜ ገደብ የሚገልጽ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማስረጃ በመያዝና የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብቻ ሲዳማ ባንክ በኮሌጁ ስም በተከፈተው የሂሣብ ቁጥር 3428302000039 ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ተከታታይ ቀናት በይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ አስተዳደር ህንፃ ላይ ባለው በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸውን በግልፅ በመሙላት በማኅተምና በፊርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። የሚሞላው ዋጋ (15%) ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 /ሃያ ሺህ/ ብር በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማዘጋጀት ኦርጅናል እና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች ካሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 30% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡
5. ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል የማይዋዋል ከሆነ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
6. ተጫራቾች ያሸነፋትን የጣውላውን ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ መጓጓዣ እስከ ኮሌጁ የሚያቀርብ ሲሆን ማንኛውም ወጪ በተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል።
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በታወጀ በ11ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያውኑ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በመክፈቻው ሰዓት የማይገኙ ከሆነ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም። የጨረታው መክፈቻ ቀን ወይም 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
9. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር-046-225-15-62 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ክህሎት ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የይርጋዓለም ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
