በሲዳማ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሀዋሣ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017/2018 በጀት አመት የፅ/መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮምፒዩተር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Sidama Region Agriculture Research Institute (የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 071/2018
በሲዳማ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሀዋሣ ግብርና ምርምር ማዕከል በ2017/2018 በጀት አመት የፅ/መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አነስተኛ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ኮምፒዩተር በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
1. በሥራ ዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የ2017/2018 ዓ.ም የመንግሥት ግብር አጠናቀዉ ስለመክፈላቸዉ ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
2. ተጫራቾች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተካተቱ መሆን አለባቸዉ፡፡
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢዎች ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. አንዱ ተጫራች ሌላ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
5. ተጫራቾች ለጨረታው ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕከሉ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳብ /ዋጋ/ በመሙላት እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በማዕከሉ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ማዕከሉ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ያስረከባል፡፡
9. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በመንግሥት የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡30 11ኛው ቀን በመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ በማዕከሉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
• ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
• ለበለጠ መረጃ - 0911738584
የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት
