Tender Detail

Tender Details

  • Company Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)
  • Address ወራቤ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046-771-06-88
  • Website
  • Deadline02 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-02 00:00:00
  • Categories Furniture And Furnishing , Electronics Materials , Educational And Training Equipment And Machinery

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ/ም በዩኒሴፍ ድጋፍ አዲስ ለሚቋቋሙ 6 የልዩ ፍላጎት አካቶ የትምህርት መስጫ ማዕከላትን ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Central Ethiopia Region Bureau of Education (የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 006

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ/ም በዩኒሴፍ ድጋፍ አዲስ ለሚቋቋሙ 6 የልዩ ፍላጎት አካቶ የትምህርት መስጫ ማዕከላትን ለማደራጀት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ግዥ ለመፈጸም

1.     የአካል ድጋፍ መርጃ መሳሪያዎች፣ 2. የሞንቶሶሪ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች በETOL (plorR) እና በዩኒሴፍ ድጋፍ፣ 3. የሞንቴሶሪ ሸልፍና ፈርኒቸሮች፣ 4. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በETOL (plore) በዩኒሴፍ ድጋፍ እና በመደበኛ በጀት ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 01 የትምህርት የአካል ድጋፍ መርጃ መሳሪያዎች፣

ሎት 02 የሞንቶሰሪ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣

ሎት 03 የሞንቶሰሪ ሸልፍና ፈርኒቸሮች፣

ሎት 04 የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ግዥ፣

1.     በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍታድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያሳደሱ በግብር ከፋይነት ተመዝግበው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት እንደዚሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡበትን መረጃ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

2.     ተጫራቾች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ ለሥራው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናሻል እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው አሽገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.     ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወራቤ ከተማ ክልል ትምህርት ቢሮ ግዥና ንብረት አስ/ዳይሬክቶሬት ማቅረብ አለባቸው፡፡

6.     ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን 8:00 ታሽጎ በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡

7.     የውል ማስከበሪያ - የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ7 ቀናት በኋላ ውሉን መፈረምና የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች ክፍያ በሚፈጸምበት የገንዘብ አይነት የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ አለበት፣

8.     ቢሮው ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታው ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በጨረታው ውድድሩ በአሸናፊው የተሰጠው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡

9.     የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆየው ለ45 ቀናት ብቻ ነው።

10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0467710688 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት- ትም/ቢሮ

Save Tender