Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
  • Address ሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 418 : ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251916866043
  • Websitehttps://www.sidamanrsps.gov.et/
  • Deadline03 Apr 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-04-03 00:00:00
  • Categories Computer Laptop And Accessories , Office Machines And Computers

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክስቴሸን /Work-station/ ኮሚፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)


በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 16 24.

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክስቴሸን /Work-station/ ኮሚፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም፡-

•        ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

•        ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል፡፡

•        ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ/ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

•        የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ዉስጥ ከተዉ በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት 10ኛዉ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

•        ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛዉ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ቦታ ከቀኑ 4፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታዉን ከመከፈት አያግደዉም፡፡

•        የጨረታው መዝግያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀዉ ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

•        ተጫራቾች መመሪያ ባለማከበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ሀላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል፡፡

•        ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን የሚያካትት መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

•        አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፊ አለባቸው። በቁጥርና በፈደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካል ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡

ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Save Tender

መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/ የግልጽ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ፡ ኮምፒውተር እና የኮምፒውተር መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕ...

READ MORE