Tender Detail

Tender Details


በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

ኦላይን የግልጽ ጨረታ ቁጥር AE001/2018

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡- በግልጽ ጨረታ ቁጥር AE001/2018 በ21/07/2018 የተለያዩ ሞባይል ቀፎዎች፤ ቴሌቪዥን፤ ፍሪጆች፤ ያገለገለ እስፔርፓርት፤ የግንባታ ዕቃዎች በኦላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈግ ማንኛውም ተጫራች

1.     በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።

2.     ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድእነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው፡፡

3.     በግልጽ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ ኦላይን መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ እና የዕቃዎቹን ሳንኘል ማግኘት ይችላሉ፡፡ እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

4.     ጨረታው የሚካሄደው ሙሉ ለሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ነው።

5.     ለግልጽ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን ለለበት፡፡

6.     በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) (CUSTOMS COMMISSON DIREDAWA BRANCH OFECE) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7.     ተጫራቾች ግልጽ ጨረታ ኦንላይን ከሆነበት ከ14/07/2018 4:00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 21/07/2018 4:00 ሰዓት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡

8.     በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ይሆናል።

9.     አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሽናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለፁት ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች ለጨረታ ማስከበረያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለጨረታ ይቀርባል፡፡

11. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 0905115511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0915460970 (0912885746) መደወል ይቻላል።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender