በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶ ማንሻ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
South Ethiopia Region Revenue Bureau (የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፎቶ ማንሻ ካሜራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ
5. በEGP የአቅራቢነት ምዝገባ የተዛባ ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር ለኤሌክትሮኒክስ 200 በመክፈል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 9 ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ማግኘት ትችላላችሁ።
7. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ለኤሌክትሮኒክሱ 15,000 ብር ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
8. ተጫራቾች ከላይ ከ1-7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ቁጥር 9 ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ማስገባት ይችላሉ።
9. የጨረታው አሸናፊው ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ እስከ ደቡብ ኢትዮጵያ ከልል ገቢዎች ንብረት ከፍል አምጥቶ ማስረከብ አለበት።
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የመንግስት ሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥን በ15ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ወይም የመንግስት ሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል ማለት ነው።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የስልክ ቁጥር፡- 0964 935 747 / 0916 698 994
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ
