Tender Detail

Tender Details


ልሕቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ልሕቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባሕርዳር ኢትዮጵያ


በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሠነድ ቁጥር፡- ልዲቁኮ-11/2018

 

ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማለትም፡-

1.     የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

–        ላፕቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 67

–        ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 04

–        Digital Bill Board.

–        NAS /Network Attached Storage እና ሌሎች ተዛማጅ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፤

2.     ለሲቪል፡ ሳኒተሪ እና ኤሌክትሪክ ስራዎች የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ የግንባታ ግብዓቶችን እና

3.     250 ግራም የልብስ ሳሙና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

2.     ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህር ዳር በግዥና ንብ/አስ/ቡድን የስራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 08 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላል።

3.     ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ሰዓት ላይ ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉቡት ይከፈታል።

4.     ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በሲ.ፒ. ኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 ማቅረብ ወይንም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።

5.     ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 058-218-02-73 ሞባይል 0918-08-55-89/09-96-14-20-56 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50 በመላክ መጠየቅ ይቻላል።

 

ልሕቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ባሕርዳር ኢትዮጵያ

Save Tender