የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
LeDeG Midwifery College Charity Organization ( LMCCO ) (የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (NCB 003/2018)
የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 14 ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበርዝቅ ብሎ ከበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጐት ድርጅት ዲን አፊስ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ከዚህ በታች በሰንጠረገዡ መሠረት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ በለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጐት ድርጅት ስም ሞልተው ከኦሪጅናል የመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታው መለያ ቁጥር |
የጨረታ ማስከበሪያ (በብር) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
||||
|
1 |
ዲስክ ቶፕ ኮምፒዩተር |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
|
2 |
ላፕቶፕ ኮምፒዩተር |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
|
3 |
ታብሌት ኮምፒዩተር |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
|
4 |
ዲቫይድር |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
|
5 |
ዩፒኤስ |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
|
6 |
ስታበላይዘር |
NCB 003/2018 |
3,000.00 |
በ15ኛው ቀን |
4፡30 |
በ15ኛው ቀን |
4፡45 |
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የመወዳደሪያ ሰነዶች ቴክኒካል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሺያል አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ ለየብቻው አሽገው የጨረታውን ስምና ቁጥር በመፃፍ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ተከታታይ ቀን ጀምሮ በሰንጠረዡ መሠረት በኮሌጁ ዲን ኦፊስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጡ ተጫራቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ስድስት ኪሎ ከመርሃ ዕውራን ማህበር ዝቅ ብሎ በበላይ ዘለቀ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ የበጐ አድራጎት ድርጅት ዲን ኦፊስ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ ወይም ቅዳሜና እሑድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታዎች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚያገኙ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ
በስልክ ቁጥር 0955 -11-11-11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
7. ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የለደግ ሚድዋይፈሪ ኮሌጅ
