Tender Detail

Tender Details


የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት፡-

ተ.ቁ

የሎት ዝርዝር

የግዥው ዓይነት

1

ሎት 1

የጽሕፈት መሣሪያ

2

ሎት 2

የጽዳት ዕቃዎች ግዥ

3

ሎት 3

የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች

4

ሎት 4

ለልብስ ስፌት ማሰልጠኛ የሚያገለግሉ ዕቃዎች

5

ሎት 5

ጄኔሬተር

 

•        በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

•        ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጣቸውን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

•        ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ለሎት1፣4፣5 እና ለሎት3 ለእያንዳንዳቸው ብር 150,000 (አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 2 ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፤

•        ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀው የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀናት 11፡30 ሰዓት ድረስ ለሎት1፣4፣5 እና ለሎት ብር 400 (አራት መቶ) ሎት 2 ብር 300 (ሦስት መቶ) የማይመለስ በመክፈል ከቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ ይችላሉ፡፡

•        ተጫራቾች የማጫረቻ ሰነድ /ፕርፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና የፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ኦርጂናልና አንዳንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግና ሲፒአ ወይም ቼከ ወይም ደግሞ የባንክ ጋራንቲ ቴክኒካልና ኦርጂናል ዶክመንት ውስጥ በመከተትና አጠቃላዩ በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

•        የጨረታውን ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸግም የመከፈት ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ፣ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል።

•        ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ዱራሜ ከምባታ ዞን መንገድ ልማትና ትራንስፖርት መመሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ፣

በስልክ ቁጥር፡- 046 554 18 32፣ 09 10 03 33 19፣

09 16 28 42 15፣ 09 23 06 29 49፣

09 12 24 36 44፣ 09 26 09 80 67

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ቢሮ

Save Tender