በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ባለው በጀት የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መ/ስ/ኮ/ግ/ጨ/003/18
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም ባለው በጀት የተለያዩ የፅህፈት ዕቃዎች እና የፅዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቶች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች -
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን እና የግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ የግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
3. ፍላጐት ያላቸው ብቁ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ የሚችሉት እና የጨረታ ሰነዱ የሚመረመርበት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ነው።
4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል የተሟሉና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
5. ሰነዱ የሚሸጥበት እና ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ- መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ ወደ ሰመራና ሀረር መገንጠያ ከባድ ጭነት ሚዛን ፊት ለፊት ግዥ ዴስክ ቢሮ፡- እስከ 14/7/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ አዋሽ ሰባት ኪሎ በ14/7/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ14/7/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
7. ንብረቱን ገቢ የሚያደርጉት በመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ ንበረት ግ/ቤት አዋሽ ሰባት ኪሎ ነው፤ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘወትር በ033-540-06-19 ይደውሉ።
8. መለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የመለስተኛ ስታፍ ኮሌጅ
