የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ለ 3 አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
የቢሮ ኪራይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ለድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ህንጻ ለ 3 አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም - በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ
የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የይዞታ ማረጋገ ካርታ እና የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማስረጃ ማያያዝ የሚችሉ እና መብራት ውሃ የተሟላለት መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአስተዳደሩ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው የክፍሎች ብዛት እና ስፔስፊኬሽን መሰረት መሆን ይኖርበታል። የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛ ቀን 11፡30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን 8፡30 በዋናው መስሪያ ቤት ሲሆን አሸናፊው ሲለይ ውል ለመፈጸም ዝግጁ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለኪራዩ የሚቀርበው ዋጋ VAT ማካተትና ያለማካተቱን መግለጽ ይኖርበታል።
የሪጅን ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉበትን ለቢሮ የሚሆነውን ቦታ እና መረጃ የመስጠት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
ከአስፋልት ወይም ከዋናው መንገድ ገባ ያለ ከሆነ 500 ሜትር መብለጥ የለበትም። ከዋና መንገድ ገባ ያለ ከሆነ እስከ ስፍራ ድረስ የአስፋልት፣ የጠጠር ወይም የኮብል እስቶን ንጣፍ መንገድ ያለውና በቂ የጥበቃ ክፍሎች ያለው መሆን ይኖርበታል።
አድራሻ - ድሬዳዋ ከተማ ግንደ ቆሬ ፎዚያ ሕንጻ ድሬዳዋ ጤና ቢሮ አጠገብ
ስልክ - 0251124735 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
