በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ግብአቶችን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው ሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ግብአቶችን በጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
1. የደንብ ልብስ
2. የመስኮት መጋረጃ ስፌት
3. አላቂ እቃዎች
4. ቋሚ እቃዎች
5. ህትመቶች
6. መድሃኒቶች
7. ሪኤጀንቶች
8. የጽዳት እቃዎች
9. ጥገና (የኮምፒውርና ፕሪንተር የላውንደሪ ማሽን፤ የፎቶ ኮፒ ማሽን)
10. የጀነሬተር ሰርቪስ በግልጽ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልግ ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፋይ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ፣
2. ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር /200 ብር/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰአት በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ከፍል ቢሮ ቁጥር 413 መግዛት ይቻላል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ለእያንዳንዱ ማለትም ለአላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ለጽዳት እቃዎች፣ ለቋሚ እቃዎች፣ ለመድሃኒት= 3,500.00 (ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ኦርጂናልና ኮፒውን ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 413 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ለማይቀርብባቸው እቃዎች እስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
7. ሲፒኦ (CPO) የሚያያዘው ኮፒው ላይ መሆን አለበት።
8. አሸናፊው የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
9. ኦርጅናል ፖስታዎችን በጨረታ መክፈቻ መወዳደር ወቅት የማይከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።
10. የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ይሆናል።
11. ጨረታው ለ10 የስራ ቀን ከቆየ በኋላ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው ዕለት ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በህይወት አምባ ጤና ጣቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
12. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
ማሳሰቢያ፤ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ በቂርቆስ ክ/ከተማ ህይወት አምባ ጤና ጣቢያ ፋይናንስ ክፍል ልዩ ቦታው ከቡልጋሪያ ማዞሪያ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ አጠገብ በስልክ ቁጥር 0114706040 መደወል ይቻላል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ የሕይወት አምባ ጤና ጣቢያ
