Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)
  • Address የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አ/አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ላንቻ አካባቢ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913 108 990
  • Websitehttps://oromiapolice.gov.et/am/
  • Deadline30 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-30 00:00:00
  • Categories Car Decoration Materials , Tire And Spare Parts , Vehicle tire , Vehicle Spare Parts

የኦሮሚያ ፖሊስ በ2018 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች ለመግዛት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Oromia Police Commission (የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን)


የጨረታ ማስታወቂያ በኦሮሚያ ፖሊስ የተዘጋጀ

ግ/ጨ/04/2018 የበጀት ዓመት

 

የኦሮሚያ ፖሊስ በ2018 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና መለዋወጫዎች እና የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች ለመግዛት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ኦሮሚያ ፖሊስ የሚገዟቸው ከዚህ በታች ቀርበዋል።

በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-

ሎት አንድ፡- የመኪና ጎማዎች

ሎት ሁለት፡-የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች

ሎት ሶስት፡- የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች

በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።

1.       ተጫራቾች ህጋዊ የ2018 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤

2.       የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸዉ የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

3.       በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

4.       ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስዙት የጨረታ ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ማቅረብ የሚችል።

5.       የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ ለየብቻ በማዘጋጀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

6.       ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ለየብቻ አሽገው ማቅረብ አለባቸው። እንዲሁም በ2 /ሁለት/ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በመለየት በአጠቃላይ በ4 /አራት/ ፖስታ ማለትም ቴክኒከል ኦርጅናል፤ቴክኒከል ከፒ፤ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ፋይናንሻል ኮፒ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ በማሸግ ማስገባት አለባቸው።

7.       የጨረታ ሰነዱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል መግዛት ይችላሉ።

8.       አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጎጎያዣ፤ መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅበታል።

9.       ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ሲያዘጋጅ ቫትን ጨምሮ ማንኛውንም ወጭን ጨምሮ ማዘጋጀት አለበት፣ ይህ ካልሆነ ግን በተጫራቹ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ማንኛውንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።

10.   ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነገደብ 21/07/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።

11.   ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 21/07/2018 ዓ.ም በግዥ መምሪያ ቢሮ ውስጥ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

12.   የኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፡-

አድራሻ፡-ኦሮሚያ ፖሲስ ኮሚሽን አ/አባበ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አከባቢ

ለተጨማሪ መረጃ እና ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 0913108990 ወይም 0996054778 መደወል ይችላሉ።

 

 

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

Save Tender