የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክስቴሽን /Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ (Sidama National Regional Government Government Communication Affairs)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 1480
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ወርክስቴሽን /Work-station/ ኮምፒውተር በዘርፉ ከተሰማሩ ብቁ ከሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
• ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
• ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ የውል ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በሕጋዊ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በማዘጋጀት ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታዎችን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታ መመሪያ ጋር አባሪ ተደርጎ ተያይዟል፡፡
• ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
• የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በታሸገ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ከተው በሁሉም ዶክመንት የድርጅቱን ማህተም በመምታትና በመፈረም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 እስከ 4፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
• ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10ኛው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 4:30 ታሽጎ ከጠዋቱ 5:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
• ጨረታው መዝግያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡
• ተጫራቾች መመሪያ ባለማክበራቸው የሚፈፀም ማንኛውም ስህተት ኃላፊነቱ የተጫራቾች ይሆናል።
• ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታከስን የሚያካትት መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
• አቅራቢዎች ጠቅላላ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመመጣጠን ካለ በፈደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ቢሮው የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ሁለተኛ ፎቅ በስተግራ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
