ሻይኒ ዴይ ሶሻል ሰርቪስስ ኦርጋናይዜሽን እ.አ.አ. የ2025 ዓ/ም በጀት ዓመት ሂሳብ የወጪ ደጋፊ ሠነዶችን ህጋዊ በሆነ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል።
Shiny Day Social Services Organization (SDSSO) (ሻይኒ ዴይ ሶሻል ሰርቪስስ ኦርጋናይዜሽን)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሻይኒ ዴይ ሶሻል ሰርቪስስ ኦርጋናይዜሽን መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት በ1998 ዓ/ም የተመሰረተ ሲሆን ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣልን በምዝገባ ቁጥር 2162 ተመዝግቦ የተለያዩ የማህበረሰብ ልማቶችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ እ.አ.አ. የ2025 ዓ/ም በጀት ዓመት ሂሳብ የወጪ ደጋፊ ሠነዶችን ህጋዊ በሆነ ኦዲተር ማሰራት ይፈልጋል።
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ኦዲት የማድረግ ፈቃድ ያለው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣
3. የወቅቱን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃና የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችል፣
4. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሥራውን ሰርቶ ለመጨረስ የሚፈጀውን ጊዜና ዋጋ ቫቱን ጨምሮ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በፖስታ ሳጥን ቁጥር 1825 ሀዋሳ በመላክ ወይንም በግንባር በመቅረብ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0910170951 ይደውሉ።
ሻይኒ ዴይ ሶሻል ሰርቪስስ ኦርጋናይዜሽን
