Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Industrial Parks Development Corporation (SEIPDC) (የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)
  • Address አርባምንጭ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 04621814411
  • Websitehttps://southethiopiaipdc.org/
  • Deadline14 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-14 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

South Ethiopia Industrial Parks Development Corporation (SEIPDC) (የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን)


ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-NCB-SE IPDC 001/18

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለ2018 በጀት ዓመት ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚውል

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1.     የዕቃው አይነት

•        በሎት 1. የጽህፈት ዕቃዎች

•        በሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች እና

•        በሎት 3. የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች

2.     በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሕጋዊ ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

4.     ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

5.     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ ይቆያል።

6.     የጨረታ ሰነድ በኮርፖሬሽኑ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት በአርባ ምንጭ ከተማ በግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ተኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታውን በቀጣይ የሥራ ቀን በተሰጠው ሰዓት ይከፈታል። ዘግይተው የሚመጡ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡

7.     ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው ውል ባለመፈጸም የታገዱ መሆን የለባቸውም።

8.     የጨረታ ሰነድ በጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ኮርፖሬሽኑ ድረስ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

9.     ተጫራቾች በዕቃው መመዘኛ መሠረት በዓይነትም ሆነ በመጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሣተፍ ይችላሉ።

10. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በኮርፖሬሽኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

11. አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት የማይተገብር ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይሆናል።

12. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ ኮርፖሬሽኑ ተጠያቂ አይሆንም።

13. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተንተርሶ ሌላ ዋጋ መስጠት ክልክል ነው።

14. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃዎቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን ይኖርበታል።

15. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገጽ ላይ ስም፣ ፊርማ ማህተም፣ ሙሉ አድራሻቸውን ማኖር አለባቸው።

16. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ለሚኖራቸው ጥያቄ እና ማብራሪያ የጨረታ ጊዜው ከመጠናቀቁ 4 ቀን በፊት ከታች በተገለጹት ስልክ ቁጥሮች እና አድራሻ በመደወልና በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ። ሆኖም ጥያቄው ወይም ማብራሪያው በጽሁፍ የተደገፈ መሆን አለበት።

17. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

18. የጨረታ ሰነዱ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000607480568 በኮፖሬሽኑ ስም ገቢ በማድረግ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች በአንዱ ወይም በሁሉም ሎት ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን፡- 0910203165 / 0911092168 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አድራሻ:- በአርባምንጭ ከተማ ከሪፈራል ሆስፒታል ከፍ ብሎ ባለው አንጆኖስ ሆቴል ሕንፃ ላይ ዋናው ቢሮ።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

Save Tender