Tender Detail

Tender Details

  • Company Duka Youth Led Organization (ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን)
  • Address አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08፣ በቅ/ሥላሴ ቤ/ክ በኩል ከ 4 ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ አዲስ ቪው ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው መታጠፊያ 200 ሜትር ወረድ ብሎ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ ሦስተኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0980 81 00 07
  • Websitehttps://dukayouthledorganization.org/
  • Deadline09 Mar 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-03-09 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (Duka Youth Lead Organization) እ.ኢ.አ የ2025 ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴዎቹን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና በኢትዮጵያ የታክስ ባለሥልጣን ተቀባይነት ባላቸው ኦዲተሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን አረጋግጦ ማስመርመር ይፈልጋል።

Duka Youth Led Organization (ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን)


የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

 

ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን (Duka Youth Lead Organization) በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን (ሲ.ማ.ድ.ባ) አዋጅ ቁጥር 1113/2019 መሠረት በመዝገብ ቁጥር 7471 ተመዝግቦ ወጣቶች ላይ የሚሠራ ሙሉ በሙሉ በወጣቶች የሚመራ ሀገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። ድርጅቱ እ.ኢ.አ የ2025 ዓመታዊ የሂሳብ እንቅስቃሴዎቹን በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና በኢትዮጵያ የታክስ ባለሥልጣን ተቀባይነት ባላቸው ኦዲተሮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን አረጋግጦ ማስመርመር ይፈልጋል።

1.     የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው

2.     የታደሰ የሥራ ፍቃድ ያለው እና አስፈላጊውን የመንግሥት ግብር እየከፈለ መሆኑን ማረጋገጥ የሚችል

3.     በሙያ ብቃት እና ሕጋዊነት ታውቀው በመንግሥት የተመዘገቡ

4.     ከዚህ ቀደም መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶችን የሂሳብ እንቅስቃሴ እዲት አድርጎ የሚያቅ ስለሆነም መስፈርቶቹን የምታሟሉ አመልካቾች ከላይ የተጠቀሱትን ዶከመንቶች የማይመለስ ኮፒ፣ ለምትሰጡት አገልግሎት የምትጠይቁትን የገንዘብ መጠን (ታክስን ጨምሮ) እና የዓመቱን የሂሳብ ምርመራ ጨርሳችሁ የምታስረከቡበትን ቀን በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት፤ በታሸገ ፖስታ በድርጅቱ ቢሮ ማቅረብ ትችላላችሁ።

አድራሻ፡- አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08፣ በቅ/ሥላሴ ቤ/ክ በኩል ከ 4 ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ አዲስ ቪው ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው መታጠፊያ 200 ሜትር ወረድ ብሎ አማኑኤል ኅብረት ቤ/ክ ሦስተኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ፡-

ስልክ: 09 80 81 00 07/ 09 97 34 64 38/ 09 25 53 18 95

ኢ-ሜይል፡- contact@dukayouthledorganization.org.

ወይም dukayouthledorganization@gmail.com

ማሳሰቢያ፡- በዚህ ማስታወቂያ ላይ ከጾታ ጋር በተያያዘ በወንድ የተገለጸው ለአጻጻፍ እንዲመች ሲባል እንጂ ሁለቱንም ጾታ ያካትታል።

 

ዱካ ዩዝ ሌድ ኦርጋናይዜሽን

Save Tender